ማክሰኞ 21 ኖቬምበር 2017

ኅዳር 12 ቀን ማኅሌት

                                      ኅዳር 12 ቀን ማኅሌት

እንኳን አደረሰን
በዛሬው ዕለት የምናከብረው በዓል እግዚአብሔር በመልአኩ
በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት ሕዝቡን ከግብጽ ከባርነት ቤት
በማስወጣት ወደ ተስፋ ሀገረ ወደ ከነዓን እንዲገቡ ማድረጉን
እና የእሥራኤል ዘሥጋ ነፃ መውጣትን ፣ ቅዱስ ሚካኤል
ዱራታኦስን እና ቴውብስታን ስለ መርዳቱ ፣ መስፍነ እሥራኤል
ኢያሱን ለመርዳት መገለጡን እንዘክራለን፡፡
ይህ የነጻነት በዓል ለአዲሲቷ እሥራኤል፤ የቅድስት ቤተ
ክርስቲያን መንፈሳዊ ጉዞ እና ነጻነት ምሳሌ ሲሆን፡፡ በዚያ ዘመን
እሥራኤል ዘሥጋን በመንፈሰ ረድኤት እየረዳቸው፣ በዕደ
መልአኩ እየጠበቃቸው፣ በሙሴ እየመራቸው፣ ጠላት
እያጠፋላቸው፣ ከተስፋዋ ምድር እንዲገቡ እንዳደረጋቸው ሁሉ
በግብጽ በተመሰለች በዓለም ያለነው ክርስቶሳውያን
ምእመናንንም ዐይን ያላያትን፣ ጆሮ ያልሰማትን፣ የሰው ልብም
ያላሰባትን፣ እግዚአብሔር ለባለሟሎቹ ያዘጋጃትን አማናዊት
ከነዓን ይህችውም መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ የበቃን ሆነን
እንድንገኝ በመልአክህ ኃይል ሰውረን፣ ጠብቀን፣ አድነን በማለት
ምሳሌውን በማሰብ አማናዊውን ጉዞ ደግሞ በማስቀጠል
በረከት የምናገኝበት በዓል ነው፡፡
የእሥራኤል ረዳታቸው ቅዱስ ሚካኤልም በጥበቃው በጸሎቱ
ከእኛ እንዳይለይ ፤ ርግብ በከፍታ ሥፍራ ሆና በምድር
የወደቀችውን ቅንጣት ዘር እንደምትመለከት ሁሉ ካለህበት
ሥፍራ ከዓለመ መላእክት ሆነህ እያንዳንዳችንን ተመልከተን ፤
ጸሎታችን አሳርግልን ከሰይጣንም ማታለል ጠብቀን በማለት
የምንለምንበት የተወደደች ዕለት ናት፡፡
መልክዓ ሥላሴ
1
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብዓ ሰብእ ዘኀሠሠ፤
ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤
እመ ትትሄየዩኒሰ ወተኀድጉኒ ጽኑሰ፤
ሚካኤልኑ ለአምጽኦ ሥጋየ ጌሠ
ወእመ አኮ ገብርኤል ወኀበኒ ነፍሰ፡፡
ትርጉም ፡- [አብ ወልደ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ስለ ጥልቅ ንስሐ
የተነሳሕያንን የንስሐ ዕንባ ስቴን (መጠጥ) ለሚሻ ጉርዔያችሁ
ሰላምታ ይገባል፤(ሕዝ 18፡32) ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የባለሟልነት
ባለጸጋ ናችሁና ከባለሟልነታችሁ አታውጡኝ፡፡ ከባለሟልነት
አውጥታችሁ በቸልታ ከተመለከታችሑኝማ ሚካኤል ገስግሶ
ሥጋዬን ለማስገኘት ይሆንለታልን ? ወይስ ገብርኤል በክንፉ
ከንፎ የነፍስን ሕይወት ሊሰጠኝ ይቻለዋልን ክሂሎት የእናንተ
ብቻ ነው፡፡]ጐሥዓ ልብየ ጥበበ ወልቡና ፤
ዚቅ
አመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር፤
ኢዜነዎ ለሰማይ ወኢተማከረ ምስለ መላእክቲሁ፤
ወተከለ ሠለስተ ዕፀ ሕይወት በዲበ ምድር፤
እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ፤
ዘሠናየ ጽጌ ደንጐላት ወጥዑመ ይፈሪ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፡፡
ነግሥ
2
ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤
ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና ፤
አንተኑ ዘመራሕኮሙ ፍና፤
ወአንተኑ ለእሥራኤል ዘአውረድከ መና፤
ዚቅ
አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፤
ፀዓዳ ከመ በረድ ወርእየቱ ከመ ተቅዳ፤
ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፤
አውሐዘ ሎሙ ማየ ሕይወት፤
ዘትረ ኰኵሕ ፈልፈለ ነቅዓ ዘኢይነጽፍ ፤
ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፡፡
3
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤
ወልደ ያሬድ ኄኖክ በከመ ጸሐፈ ፤
ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤
ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤
ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ፡፡
ትርጉም ፡- [ የያሬድ ልጅ ኄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም
አጠራር ጋር ለተባበረ ስምህ አጠራህ ሰላም እላለሁ፡፡
የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ ሆይ የተቸገረቱን የተጨነቁትን
ዘውትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን
ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልኝ፡፡]
ዚቅ
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል ፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤
ይሰአል ለነ ረዳኤ ይኩነነ አመ ምንዳቤነ፤
ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ፡፡
3
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተሀበለ ፣
በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበሀለ
ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ
ቀዊምየ ቅድመ ሥዕልክ ሶበ አወትር ስኢለ
በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዐኒ ቃለ፡፡
ትርጉም ፡- [ስለ ሙሴ ሥጋ ከሰይጣን ጋር ክርክር በተደረገ
ጊዜ የዘለፋን ቃል ላልተናገረው አንደበትህ ሰላም እላለሁ፡፡
ክቡር መልአክ ሆይ ክብርህ ከመላእክት ሁሉ ክብር ከፍ ያለ
ነውና፤ በሥዕልህ ፊት ቁሜ ልመናዬን በማቀርብበት ጊዜ ሁሉ
እሽ በማለት ፈጥነህ ቃልህን አሰማኝ፡፡] (የሐዋርያው የቅዱስ
ይሁዳ መልእክት ቁ. 9)
ዚቅ
ረሰዮ እግዚኡ ፡ ለውእቱ ሚካኤል ፤
እምኵሎሙ መላእክት ይትሌዓል መንበሩ ፡፡
4
ሰላም ለሕንብርትከ፡ ሕንብርተ መንፈስ ረቂቅ፤
ዘቱሳሔሁ መብረቅ፤
ነግሀ ነግህ አንተ በአዝንሞ መና ምውቅ ፤
በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ፤
ሴስየኒ ሚካኤል ሕገከ ዘጽድቅ፡፡
ዚቅ
ባሕረ ግርምተ ፡ ገብረ ዓረፍተ ወበውስቴታ አርአየ ፍኖተ፤
በእደ መልአኩ ዓቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርብዓ ዓመተ፤
ወሴሰዮሙ መና ኅብስተ ፡ ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ ዘአልቦ
መስፈርተ፡፡
5
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤
ለለ አሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ፤
ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤
ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤
ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ፡፡
ትርጉም ፡- [ ሚካኤል ሆይ ለእያንዳንዱ በየ ክፍሉ ለተነገሩ
መልኮችህ ሁሉ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርባለሁ፡፡ ልዑል
መልአክ ሆይ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽብህ ኃያል
መልአክ ነህና የምስጋናዬን እጅ መንሻ ተቀብለህ ከላይ
ከኢየሩሳሌም ሰማያዊት የጸሎቴን ዋጋ እጥፍ ድርብ አድርገህ
ላክልኝ፡፡]
ዚቅ
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፤
ወስእለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፤
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፡፡
+++
ምልጣን
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል ፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤
ይሰአል ለነ ረዳኤ ይኩነነ አመ ምንዳቤነ፤
ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲ
እስመለዓለም
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል
አስተምር ለነ ሰዓልናከ በአሰርቱ ወአርባእቱ ትንብልናከ
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል
ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል
ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ስርየት ለኀጥአን
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ክቡር መኑ ከማከ ልዑል
ሰላም
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል፤
ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ

ቅዳሜ 20 ኦገስት 2016

በእውኑ ነገ ሠላማዊ ሠልፍ እወጣለሁን ?


በእውኑ ነገ ሠላማዊ ሠልፍ እወጣለሁን ?

የዛሬ ጥያቄዬ ነው
ርእስ ነው
በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት በተደረጉት ማንኛውም ሰላማዊ
ሰልፎች ላይ ከታክሲና በዳቦ ቤት ከሚገኙት አስር ወይም
በጥፍ የሚበልጠውን ዳቦ ለመግዛት ከመሰለፍ ውጪ ሀገራዊ
በሆነ ጉዳይ ማንኛውንም የተቃውሞ ሰልፍ የመውጣት እድል
ገጥሞኝ አያው�ቅም በ1997 የተደረገውን ሰልፍ በእድሜ
አለመድረስና አለመምረጥ ምክንያት እድሉን አጥተናል ።
ለማንኛውም
" ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል " እንደሚባል
እንደ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ አባባል የኦሮሞ ሕዝብ ለአማራ
ለሌሎች ሕዝቦች ያበረከቱት ተረት ነው ቢሉንም ጊዜው አሁን
ይመስለኛል ።
እንግዲህ እኔንም ጨምሮ መንጋው ለነግ በእውኑ ሰላማዊ
ሰልፉን እወጣለውን ? ወይንም ሰላማዊ ሰልፉን እወጣለው
የሚል ሀሳብ አለው ።
በተመሳሳይ መንጋው ይህን ሊሆን ይችላል ፡ ነውም
ለነጻነቱ ሲል ለአደን ከወጣ ነብር እራሱን የሚከላከል የዝሆኖች
መንጋ ነው ። ወይንም ውይንም ይህንንም ይመስላል ሰሞኑን
በአዲስ አበባ ሰላሙን ለማደፍረስና ሁከት ለመንዛት የተቃውሞ
ሰልፍ ያደረጉትን ሰኦች እንቃወማለን እንደሚል የገበሬን ማሳ
ለማጥፋት እንደሚሄድ አንበጣም ይሆናል ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ነገ ስለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ
አበባ ፖሊስ በebc መግለጫ ሰጥቶል ።
ማንም ቢሆን የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት የተዘጋጁ
ተቃዋሚኦችን ብትመለከቱ ለሚመለከተው አካል አስታውቁ
የሚል (ቃል በቅል ባልገለብጠውም ) እኔ ምለው እንደ አዲስ
አበባ ነዋረነቴ የአዲስ አበባ ፖሊስን ለመተባበር "ሰላማዊ
ሰልፉ ላይ ቀይ ካርድ ይዤ እየወጣው ነው " እደግመዋለው
ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የቀይ ካርድ ይዤ " እየወጣው ነው ብዬ
በእራሴ ላይ ልጠቁም ነውን ?
ለመሆኑ በየትኛው አዋጅ ወይንም በየትኛው ሕግ ነው ሰላማዊ
የሆነን የተቃውሞ ሰልፍን ለመውጣት ፍቃድን ከሚመለከተው
አካል እሚጠየቀው ?
ምክንያቱም በነጻነት የመንቀሳ�ቀስ መብት የለኝም
ሀሳቤን በነጻነት እየገለጽኩኝ አይደለም
ላለ ሕዝብ ለጠየከኝ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ፈቃድ
ሰጥቼሀለው ማለት በነጻነት የመንቀሳቀስ መብትህን አሳጥቼህ
ነበር አሁን አንስቼልሀለው ማለት ይመስለኛል።
እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም " የወልቃይት ነገር "
ጽሁፍ
በዚሕ ጽሁፍ ፕሮፌሰር ለጽሁፋቸው መነሻ አንድ ሀሳብ ያነሣሉ "
ሚስትህን መምታት አቆምክ ...? " የሚል ያልተገባ ጥያቄ ።
አኦ ካልክ ወንጀል ሰርተሀል ያስጠይቅሀል አይ ካልክ ደግሞ
ወንጀል እየሰራህ ነው ። እንዲሁ ያሳስራል ።
የሚመለከተውን አካልም የሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ፍቃድ
መጠየቅ እንዲሁ ነው ። የሚመለከተው አካል ፍቃድ መስጠት
እስካሁን ስጨቁናቹ ነበር ። "ዶሮን ሲያታልሎት አርዝመው
አሰሮት " አይነት እንሁንላቹ ማለት ነው በአንጻሩ ፍቃድ
አልሰጠውም ማለት ደግሞ አሁንም ጨቆኝ ነኝ ማለት ነው ።
በእውኑ እኔ ነገ ሰላማዊ ሰልፍ እወጣለውን ?
የሚለውን ጥያቄ የቀሰቀሰው እንዲህ የሚል ጥያቄ በው
ለምን አልወጣውም ጊዜውስ መቼ ነው ?
ምክንያቱም ያለ መንጋው ሕብረት ምንም አይነት ለውጥ
እንደማይመጣ አምናለሁ ነገር ግን ተስፋ ለሌለው ሀሳብ
ከመንጋው መጉደል አልፈልግም ።
ስለዚህ ሕዝብ ነኝ የሕዝብ ጥያቄ ይመለከተኛል።

ሰኞ 21 ማርች 2016

መጋቢት 12 በዓለ ቅዱስ ሚካኤል

መጋቢት 12
ቅዱስ ሚካኤል
በዚች ቀን ቅዱስ ሚካኤልን እግዚአብሄር ወደ ጠንቋዩ በለአም
ላከው። እስራኤልንም ይረግማቸው ዘንድ ባላቅ በጠራው ጊዜ
አህያው በሰው አንድበት እስከ ተናገረች ድረስ አስደንገጠው
መርገሙንም ወደ በረከት መለሰው።
ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም ( ትንቢተ ዳንኤል 10፤21)
ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ
«መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት
ነው። ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ -
የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ ካ - የሚለው «ከመ» ማለት
ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው።
ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር
የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም
እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም
የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥
ክቡር ስም ነው።
የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን
ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ
እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥ «አቤቱ በአማልክት
መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት
ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት
መካከል) አንተን የሚመስል ማነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ
አንተ የከበረ ማነው?» ብሏል። ዘጸ ፲፭፥፲፩። ቅዱስ ዳዊትም፦
«አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። መዝ
፹፭፥፰።
የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን
አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም
ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን
የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና
ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን ፡፡
ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ
በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ
ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ ፤
ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን
ወገን ነህ ? አለው ፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት
አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ”(ኢያ.5፡13)
ይለናል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ
ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር ፡፡
ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ
ዲያብሎስ ይዋጋው ፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር ፡፡
ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ
ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ
ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት
ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት”(ዘጸ.23፡21)ብሎ
አስጠንቅቋቸው ነበር ፡፡
ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን
ያስረዳናል ፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ
እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ
አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል
ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ
ገልጦልን እናገኛለን፡ሰይጣን ሠራዊቱን አሰማርቶ በአሕዛብ
ነገሥታት እያደረ የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባሉ እስራኤልን
ዘወትር በጦርነት ያስጨንቃቸው ነበር።
በዚህም ምክንያት ሲወድቁ ሲነሡ፥ ሲነቀሉ ሲተከሉ፥ ሲፈርሱ
ሲገነቡ፥ ሲበተኑ ሲሰበሰቡ፥ ሲሰበሩ ሲጠገኑ ኖረዋል። በዚያ
ዘመን መጋቤ ብሉይ ተብሎ የሚታወቀው ቅዱስ ሚካኤል ነው።
እርሱም ዘወትር ከቅዱስ ገብርኤል ጋር ሆኖ ሕዝቡን ይረዳቸው
ነበርና።
ይኽንንም «ወደ አንተ የመጣሁት ለምን እንደሆነ ታውቃለህን?
አሁንም የፋርስን አለቃ እዋጋው ዘንድ እመለሳለሁ፥ እኔም
ስወጣ እነሆ የግሪኮች አለቃ ይመጣል። (ሰይጣን በግሪክ
ንጉሥ አድሮ ሌላ ጦርነት ይጀምራል)። ነገር ግን በእውነት
ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፥ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ
(ከመላእክት አለቃ) ከሚካኤል በቀር የሚያጸናኝ የለም።» ዳን
፲፥፳፩ በማለት ቅዱስ ገብርኤል ለነቢዩ ለዳንኤል ነግሮታል።
ቅዱስ ገብርኤል እንዲህ ካለ እኛስ ምን እንበል?
+" ቅዱስ ድሜጥሮስ ድንግል "+
=>ቅዱስ ድሜጥሮስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ:
በመንፈሳዊ ለዛ ከአጐቱ ደማስቆስ ጋር ያደገ የዘመኑ ደግ ሰው
ነበር:: በዘመኑ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ያለቁበት በመሆኑ
ቤተሰቦቹ የአጎቱን ልጅ ልዕልተ ወይንን እንዲያገባ ግድ አሉት::
+ቅዱስ ድሜጥሮስ የነርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ጋብቻውን
በተክሊል ፈፀመ:: የፈጣሪውን ፈቃድ ለመፈፀም ደግሞ
ከቅድስት እናታችን ልዕልተ ወይን ጋር ተስማምተው ለ48
ዓመታት በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንድ ምንጣፍና ልብስ
እየተጋሩ በድንግልና ኑረዋል::
+ቅዱስ ሚካኤልም ስለ ክብራቸው ከመካከላቸው ሆኖ ቀኝ
ክንፉን ለርሱ: ግራ ክንፉን ለርሱዋ ያለብሳቸው ነበር:: ከ48
ዓመታት በሁዋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ የግብፅ 12ኛ ሊቀ ዻዻስ
ሆኖ ተሹሞ: ምስጢር በዝቶለት ባሕረ-ሐሳብን ጽፎ ሠርቷል::
+ሰይጣን በሰዎች አድሮ ቅዱሱን ሚስት አለው በሚል ቤተ
ክርስቲያን ላይ ሁከት በመፈጠሩ ቅዱስ ድሜጥሮስ በመልዐኩ
ትእዛዝ ሕዝቡን ሰብስቦ: እሳት አስነድዶ: ከቅድስት ልዕልተ
ወይን ጋር እሳቱ ውስጥ ገብተው ለረዥም ሰዓት ጸልየዋል::
+ሕዝቡም ይሕን ተአምር አይተው: የቅዱሳኑን ንጽሕና
ተረድተው: "ማረን" ብለው በፍቅር የተለያዩት በዚሕ ዕለት ነው::
+ቅዱስ ድሜጥሮስና እናታችን ልዕልተ ወይን ተረፈ ዘመናቸውን
በቅድስና አሳልፈዋል:: በተለይ ሊቀ ዻዻሳቱ ድሜጥሮስ ብዙ
ድርሳናትን ደርሷል:: እነ አርጌንስ (Origen) ና ቀሌምንጦስ
ዘእስክንድርያ (Clement of Alexandria) የመሰሉ
መናፍቃንንም አውግዟል::
+ከጣዕመ ስብከቱም የተነሳ አርጅቶ እንኩዋ ምዕመናን
እየተበሰቡ ይማሩ ነበር:: በአልጋ ተሸክመውም ይባርካቸው
ነበር:: ቅዱሱ በ107 ዓመቱ ያረፈው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን
አጋማሽ አካባቢ ነው::
=>አምላከ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን ያሳድርብን:: ጸጋ በረከቱን
ደግሞ ያትረፍርፍልን::

ሰኞ 5 ኦክቶበር 2015

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስለእሬቻ ኦዳ አመጣጥ ከመሰረቱ... "

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስለእሬቻ ኦዳ አመጣጥ
ከመሰረቱ...
"..በስምንት ሺህ ዓመተ ዓለም አካባቢ የኩሽ ልጆች
ሴታና ኦራ ተጣልተው ታላቁ ሴታ ታናሹን ኦራን ገደለ
...እህታቸው አቴቴ የወንድሟን አስክሬን በሌሊት አንስታ
አባይ ወንዝ ዳር ቀብራ አምላኳ ሰላም እንዲያወርድ
ተማፅና የመታሰቢያ ዋርካ ተከለች። የኩሽ አምላክም
ዝናብ አዝንቦ ዋርካውን አሳደገው፣ በዚህም ሰላም ሰፈነ
..ከአርባ ዓመት በኋላ የአቴቴ ልጆች የነበሩት ቦረና እና
ባሬንቱ እንደገና ተጣሉ። ታላቁ ቦረና ታናሽ ወንድሙን
ባሬንቱን ገደለው። እናታቸው አቴቴም አምርራ አዘነች።
የልጇን አስክሬንም በሌሊት ቀብራ ዋቃ-"እግዚአብሔር/
አላህ" ዘላቂ እርቀ ሰላም እንዲያወርድላት አምላኳን
ተማፀነች። ዋቃም ለመናዋን ሰማ፣ ኦዳ እንድትተክልም
አዘዛት። ልጆቿም የሚዳኙበት አዲስ ስርዓት ነገራት።
ያንንም የሰላም ትንሣኤ ሕይወት ገዳ ስርዓት አለው።
ጥንታዊና መሰረታዊ እምነቱ ደግሞ ዋቄፈና ተባለ። ኢሬቻ
ይህ ስርዓት የሚከበርበት በዓል ነው። <<የአፍሪካዊያን
እናት አቴቴ የአምላኳን ትእዛዝና በረከት ተቀብላ በወንዙ
ዳር ለዳር ኦዳ ተከለች። ወዲያው ዝናብ ዘነበ፣ ኦዳዎቹም
አደጉ ዘላቂ እርቅ ሰላምም በልጅ ልጆቹ ሕይወት ላይ
ወረደ። ያ የቅድስቷ የኦሮሞ እናት አድባር የሰላም የእርቅ
ቀን <<ኢሬቻ>> ተብሎ ይከበራል።
(ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ቀዌሳ፤ ገዳ መፅሔት)"

ሐሙስ 13 ኦገስት 2015

የኔ መንገድና ጥያቄዬ


ከብዙዎች ዓለም ሕልም አለ ሕልማቸውን የሚያዩበት
እንቅልፍም እንዲሁ፡ ሕልማቸው የቀን ጥያቄአቸውና
ምኞታቸው ነው ስጋዊ ተስፋቸው ብዙዎች ሕልም
መመልከቻ እንቅልፍና አልጋ ይኖራቸው ይሆናል ጥቂቶች
ግን መተኛትም ማለም ሰልችቶቸዋል ምክንያቱም ሕልም
የሚረዳ ሕዝብና ሕልም የሚተረጉም �ፈጣሪ የለምና ።
በበረከት በላይነህ ድርሰት እያዩ ፈንገ�ስ እያዩ ሕልም
ከመፍታት ሕልም ማሰርን መርጦ " የተፈታ ሕልም
እናስራለን አዳሚ የልጅነት ሕልሜ ላገሬ ማልምላት
ምናምን ትያለሽ" ይላል እያዩ እብድ ነው እያዩ መጣያ ቦታ
ይልተ�ሰጠው ቆሻሻ ነው ለዚሕም ነው " ሠው እንዴት
ቆሻሻውን መጣያ ያጣል" የሚል እያዩ ለሰኦች እብድ
እንጂ ጤነኛ ነው እብድ ያለው የቀበሌው ሊቀመንበር
እንጂ ጤነኛ ነው ።
ጥቂቶቻችን ለብዙዎች እንዲሁ ነን እብዶችና ሰነፎች እኛ
ግን ጤነኞችና ብርቱኦች ነን ። የእያዩ ጥያቄ ብዙ ነው
የእያዩ ተጠያቂም እንዲሁ �ፈጣሪ፣ መንግስት ፣ ህዝብ
እንዲሁ እራሱን ነው ።
የኛም የኔም ጥያቄም እንዱሁ ነው ፍትሕን ለሚያውቅ
ሕዝብን ሁሉ ብቻውን ለሚገ�ዛ አምላክ እንደልቤ
የሚሆነው የጠላትን እጅ በእኔ እጅ ስር ከጣልክ ከቤቴ
ስመለስ መጀመርያ ያገኘሁትን መሰዋት እደርጋለሁ ብሎ
አፋን በመልካም ከፍቶ አፋን እንደከፈተ እድያ ድንግል
የሆነች ሴት ልጁን መሰዋት ካደረገ ዮፍታሄ ይልቅ
ባልጀራውን ኦርየንን አስገድሎ ሚስቱ ቤርሳቤህን እግብቶ
የዘሞተው ዳዊት ነው ።
ለዚሕም ይመሥለኛል ጥቂቶች የዝችን ዓለም ጣእምን
የሚንቁት ( አሥተውሉ ጥቂቶች እልኩኝ እንጂ ሰማእታት
አላልኩም ) ታድያ አለምን ሁሉ ለሚገዛ ለዚሕ አምላክ
ነው ጥያቄ ከዮፍታሔ ይልቅ ለአብርሐም ተለዋጭ
መስዋትን ለሰጠ ከዮፍታሔ ይልቅ ዳዊትን እንደልቤ ላለ ።
መልካምን አድርገህ ሳለ ለምን ምልካምን ሰው
ትነጥቃለህ የምል ለብዙኦች የእንዲሕ አይነት ጥያቄ እና
እርሶን ( ሴትን (ትግስትን) ) እስከ መሞሸርያ አንድ ቀን
መጠበቅ እብደት የሆነው ።
እኔ ግን እንደጽላጦስ "ከማምንበት ነገር በላይ የሚቀርበኝ
የለም "
እላለሁ
በዚሁሉ ነገር እና መሰል እንቅፋቶች እንደጥቂቶች ሕልም
ማለም ባልፈልግም እንደ አቢሜሌክ ግን ጥፋትን
ላለማየት ብዙ ዘመናትን መተኛት እፈልጋለሁ ።

ቅዳሜ 25 ጁላይ 2015

የወርሐ ሐሙሌ የመለአኩ ቅዱስ ገብርኤል ማሕሌት

የወርሐ ሐሙሌ የመላኩ ቅዱስ ገብርኤል ማሕሌት
ነግሥ
ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም፤
ለወልድ ሰላም ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤
ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም ፤
ለሰማእታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም፡፡
ዚቅ
እንዘ ሕጻን አዕበዮ እግዚአብሔር ወፈነዎ ብሔረ ጽልመት

ኢያውዓዮ ውኂዘ እሳት ፤ ለሕጻን ወሀቦ ሞገሰ ሖረ
ወገብዓ በሰላም፡፡
ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን፣
አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን፣
ልብሰ ሰማዕትና ይኩነኒ ምሕረትክሙ ክዳን፤
ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን፤
ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡
ዚቅ
ሃሌ ሉያ (3) አንቃዕዲዎ ሰማየ ጸለየ ወይቤ ቅዱስ
ቂርቆስ
እጼውዓከ እግዚእየ ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ
እስእለከ እግዚእየ ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር
እስእለከ እግዚእየ ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር
እጼውዓከ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ ፡፡
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤
ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤
ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤
አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳህል፤
እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡
ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤
ወብሥራት ለገብርኤል ፤ ወሀብተ ሰማያት ለማርያም
ድንግል
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት
ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም
መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ ፤ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ ፡፡
መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን፤
ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን፤
ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን፤
ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን፤
ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡
ዚቅ
ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ፤ ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ
መላእክት ይትዋነይዋ ፤
ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ አስተገብሩ ሐመዳ፤
ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን እስመ በጸሎተ ጻድቅ
ትድኅን ወኢትማስን ሀገር፡፡
ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ እንተ ተመትረ
እምጒንዱ፤
ሕጻን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ፤
ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ፤
ከመ ባረኮ አብርሓም ለይስሓቅ ወልዱ፡፡
ዚቅ
ሕጻን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ ፤
ወስምዖሙ አጥፍዑ ኃይለ እሳት ወቦዑ መንግሥተ
ሰማያት፡፡
ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ፤
ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ
ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ
መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ፤
ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ፡፡
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ ፤
ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት፤ ኢትፍርሂ እም ንፈጽም
ገድለነ፡፡
ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ
ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ ፡፡
በጸሎትከ ነጐድጓድ ወበስዕለትከ መብረቅ
አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ
ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ
ዚቅ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት ፤
ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር ፤
ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ መገቦሙ ወመርሆሙ፤
እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡
ሰላም ለህላዌከ ማእከለ ሰብአቱ ነገድ፤
እለ ሥዑላን በነድ፤
አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ ፤
ኀበ ተኀንጸ መርጡልከ ወዘዚአከ አጸድ ፤
ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡
በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም ወኢብድብድ በሰብእ
ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን
በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ ወኢአባረ እክል ፤
ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ
ወልደ አንጌቤናይት፡፡
ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ፤
ዓዲ ሰላም ለጠብአይከ አርባዕቱ፤
ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ፤
ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ፤
ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ፡፡
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት ሰላም ለኪ ሰላመ ወልድኪ
የሃሉ ላዕለ ኩልነ ፤
ኢየሉጣ እምነ ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ ሰአሊ ለነ
አስተምሕሪ ለነ፤
ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡
መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ፤
ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ፤
ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ፤
አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ፤
ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ፡፡
ዚቅ
ዘረዳእኮሙ ለሰማእት ወበላህኮሙ እምእሳት ፤
አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ እምዕለት እኪት ፡፡
ምልጣን
ይቤላ ሕጻን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት ፤
አዘድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ፤
እስመ ለዓለም
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ፤
አምላኮሙ ለቂርቆስ ወለእሙ ፤
በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ አርአየ ጸጋሁ ላዕለ
ሕጻን፤
ሕጻን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም፤
አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕጻን፤ ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት
ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን፤
አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕጻን፤
አኃዛ ለእሙ ዕደ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን ፤
አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕጻን፤
ወይቤላ ሕጻን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ እምዝ
ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ፤
አእኰትዎ ወሰብሕዎ፤ ወባረክዎ ለአብ፡፡
በሰማዕታቱ ጸሎት ይማረን፡፡አሜን፡፡

ሐሙስ 23 ጁላይ 2015

የመላኩ ቅዱስ ገብርኤል ድርሳን ሐምሌ

የገብርኤል ድርሳን ፡ ሐምሌ
‹‹ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል
ነኝ ›› ሉቃስ 1፡ 19
ሹም እለእስክንድሮስ ጭፍሮቹን እንዲህ ብሎ
አዘዛቸው፡፡ ሰም፣ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣የዶሮ፣
ማር፣እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል
ጨመሩበት፡፡ ጭፍሮችም ያዘዛቸውን ፈፅመው
መጥተው ያዘዝከንን ሁሉ ጨምረንበት ነዶ ፈልቷል
አሉት፡፡ ድምፁም እንደ ነጎድጓድ ይሰማል፤ ወላፈኑም
እንደ ፀሐይ ያንፀባርቃል፡፡
የፍላቱም ኃይል አስራ አራት ክንድ ያህል እየዘለለ
ይወጣል፡፡ በውስጡ የሚጣሉትን ሰዎች እዘዝ፡፡
ያንጊዜም ህፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይዘው
ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በክርስቶስ ስም ስላመኑ
በእስር ቤት አግብተው አስረዋቸው ነበርና ፍላቱ ወደ
ላይ በሚዘል በብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር
ሲወስዷቸው በዚያን ጊዜም እልፍ ከአንድ ሺህ አራት
መቶ ሰዎች እንዲወጡና በፈላው የብረት ጋን ውስጥ
የቅዱሳንን አሟሟት እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት
ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡
ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡
ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ግዜ እናት ሆይ ከብረት
ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ድንጋፄም አይደርብሽ
አላት፡፡ ነገር ግን አናንያንና አዘርያን፣ ሚሳኤልንም
እግዚአብሔር ከዕቶን እሳት እንዳወጣቸው እወቂ፤
እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡
እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ
ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ
ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትሺ፤ ይቅርብሽ አሁን
እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡
ሶስናን ከሀጢያተኞች እጅ ያዳናት እኛንም ከብረት ጋን
ያድነናል፡፡ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ ያዳነ እሱ
ያድነናል፡፡እግዚአብሔር በዚህ ብረት ጋን ውስጥ
ግዳጃችን ልንፈፅም ፈቅዶም እንደሆነ የኢዮብን
ነፃነት (ትእግስት) ልናገኝ ይገባናል፡፡ እሱ ልጆቹንና
ሚስቱን ያገኘው ገንዘብ ሁሉ አጥቶ በመጨረሻው
ሰውነቱን አጥቶ ነበርና ምንም ምንም የቀረበለት
አልነበረምና እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ከማለት
በቀር ያለው ነገር የለም እግዚአብሔር ሰጠ፤
እግዚአብሔርም ወሰደ አለ፡፡ እግዚአብሔርም ሆነ፡፡
የእግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም ይመስገን አለ፡፡
እኛም ይህንን መከራ ልንታገስና የተጠበቀልንን
ልንከተል ይገባናል፡፡ በዚህም ምክር እናቱን
ለማፅናናት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን
ወደሰማይ አቅንቶ ተመለከተ፡፡
እግዚአብሔር ሆይ ይህችን ባርያህን ከሰጠ
ከህይወት መፅሐፍ እኔን ፋቀኝ አለ፡፡ አቤቱ ይህነን
ነገር ልታደርግ አይገባህም፤ አቤቱ እርሻውን
ልታቃጥል ፍሬውንም ልትባርክ ትወዳለህን፡፡
አቤቱ እንጨቱን ቁረጡና አንድዱት ቅጠሉን ጠብቁ
ብለህ ልታዝ አይገባህም፡፡ እንጨቱንም ቅጠሉንም
ጠብቁ ብለህ እዘዝ እንጂ ይህ አይገባህም ያመነብህ
ሁሉ ይህን ያየ ዘንድ፡፡ ማዳን የሚችል አምላክ
ኑሮአቸው ቢሆን ከዚህ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ
እንዳይጠራጠር፡፡
ዲያብሎስ ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ
ቅዱሳኑም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ፡፡ ይህንን
ፀለየ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማሁ እንዳይል አቤቱ
የኃይል መንፈስ ለናቴ ስጣት አበርታት፡፡በዚያን ጊዜ
ዲያብሎስ ከሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት
እናቱ እንዲህ አለች፡፡ በመንግስተ ሰማያት አባት
የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ስጠኝ፡፡
የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንንሳ
አለችው የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ
በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ ቅዱሳንም
ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ
ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም
ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ስርንም
የሚበጥስ መሳሪያ አለበት፡፡
ከዚህ በኋላ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ
ወረደና የብረት ጋኑን እሳት አጠፋው ከቅዱሳንም
አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና
መፍላቱ ፀጥ አሉ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢያታቸውን
ይቅር ይላቸው ዘንድ ለኃጥአንም ወደ እግዚአብሔር
ይፀልይላቸው እኛም በየወሩ በዓሉን እያከበርን ይህን
ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤልን አማላጅ ወዳጅ
እናድርገው፡፡
ሹም እለእስክድሮስም አስራ አራት የተሳሉና የጋሉ
ብረቶች ያመጡ ዘንድ ዳግመኛ አዘዘ፡፡ ሰባቱን በእናቱ
አካል ሰባቱን በሱ አካል ውስጥ ይተክሉ ዘንድ
ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዓይኖቹ ሁለቱን
በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይተክሉ ዘንድ፡፡
ያንግዜ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ
ወረደና እሳቱን አጠፋው እሳቱም እንደ በረዶ ቀዘቀዘ፡፡
ዳግመኛም የሕጻኑን እራስ ከነቆዳው ገፈው በእሳት
ውስጥ ይጨምሩ አንድ ሹም አዘዘ፡፡ ዳግመኛው
መልአክ መጥቶ ይህንን መከራ ከሱ አራቀለት፡፡
ዳግመኛም በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ
እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ከዚህም መልአኩ አዳነው፡፡
ልመናው አገልጋዩ ይጠብቀው፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን!!