የኔ መንገድ

                              ለናትየተላከመልክት

 


#ለናትየተላከመልክት
እንዴት ነሽ እናት ያለም
ይሕየው እኛ የሚወራልሽን
አንቺነት በጉጉት እየጠበቅን አለን
እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ እናት ዓለም
አንቺም ስመ እታለም
ነፃነቱ ተመቸሽ
ወይንስ ሰለቸሽ
ይልቅስ ልንገርሽ
ተረት ነው ነፃነት
እንደሚያወሩት ፕሮፖጋንዳ ባዶነት
በርግጥ ተረት ነው ነፃነት
ከብዙ ዘመን በሇላ ለሰው
የሚነግሩት ተረት
ከብዙ ዘመን በሇላ ከመስራት ማረፍ
ከመታሠር መፈታት
ከዚሕ ሁሉ በሇላ ተረት
የተረቱ ባለቤት
ተበዳይ የተረቱ (ነፃነቱ ) ፈጣሪ በዳይ ሚሆኑበት
እናም ነፃነት ማለት
እናም ተረት ማለት
ከዘመናት በሇላ ለሠው የሚነግሩት
በባዶ መሬት ላይ የተዘራ ውሸት
እናም ተረት ማለት
ከስራ በሇላ ያለ መልካም እረፍት
ከእስር በሆላ ያለ መፈታት
ግን ሙሉ በሙሉ ውሸት
እናም ተረት ማለት ነው ነፃነት ::
ደግሞ መድፍ አስተኮስሽ
ሻማ አስገዛሽ ለልደትሽ
እኔን በረሐብ አያስጨረስሽ

------------------------
#የግርጌማስታወሻ
ሀሳብ
ከኢፍሬም ስዩም
#ማንዴላግጥም
ቅንጭብ
ይልቅስ ልንገርሕ
ተረትነው ነፃነት
ነፃነትን ነፍጎ
ኖቤል ሸላሚነት

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ