ውዳሴ



ውዳሴ ዘ አሉላ


አራስ አሉላ ሀሙሌ 3 ቀን1878 ዐም የጣልያንን ምፅዋ ላይ መስፈር በሰሙ ጊዜ የፃፉት ደብዳቤ

ከ ራስ አሉላ ዝውዕቱ ቱርክ ባሽ ይድረስ ለክቡረ ማርኮ ፓሊቤይ


ኢጣሊያኖች መጥተው ምጥዋን ሲይዙት ለምን አታባርሩዋቸውም እኔስ ለግብፅ ንጉስ ለካዲቭ ከበሬታ ብዬ ነው እንጂ በኢትዮጺያና በምጥዋ መካከል ያለውን በር እዘጋው ነበር እናንተስ ቢሆን እንደምን ፈቃድ ሠጠዋችሁ አሁንም አባሮቸው ይሕችም ሥፍራ የኢትዮጺያ ግብአት መሆኖን ኢጣሊያኖች እንዲቀመጡ አለመፈቀዱን በስመ ንጉሠ ነገስት ዩሐንስ አስታውቃችኈለውና ወደ ሀገራቸው ይመለሱ

ሀሙሌ 3 ቀን1878 ዐም

በሇላ ላይ 1879 ዐም በጣሊያን እቢተኝነት ምክያት በተደረገ ጦርነት ረስ አሉላ ጦርነቱን አሸንፈው በተመለሱ ጊዜ እንዲህ የሚል ግጥም ተገጠመላቸው ...

. . . አባ ነጋ አሉላ ካስመራ ቢነሳ
እንዳበሳ ሆኖ እሳት እያገሳ
የችግር ምስጋና ባይነሳ
ቢቸግረው ጣሊያን አለ ፎርሳ ፎርሳ . . .


. . . ተው ተመከር ጣሊያን ይሻልሀል ምክር
ሰሐጢ ላይ ሆነሕ መሬት ብትቆፍር
ሆላ ይሆንሀል ለራስህ መቃብር . . .

ዛሬ ጀግና ለመፍጠር የትላንት ጀግኖችን እናወድስ

ውዳሴ ዘ አሉላ

ምንጭ የኢትዮጺያ ታሪክ
ከተክለፃድቅ መኩሪያ

ሠላም

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ