ቤተ ፍልስፍና

ለሰው የማይመከር ሀሳብ
  
 የሠው ልጅ ተስፋ ከሚያደርገው መንግስተ ሠማያት በተቃራኒ ሀጢያት ለሰራ ወይም እንደ ቤተክርስትያን አባቶች አስተምሮ በደል የፈፀሙ ሰዎች ስጋቸውና ነፍሳቸው ስለሚቃጠልበት ቦታ ሲኦል እንደ ቤተ ክርስትያን አባቶች አስተምሮ ፍፁሞ አስፈሪ ተደርጋ ትሳላለች ከቀደምት ታሪኮች አንፃር. ..

አጥኑ ነዌ ስለበደሉ ብዛት በሲኦል እያለ በሲኦል ስላለው መከራ ስለ 6 ወንድሞቹ ፀለየ ይሕም ማለት በሲኦል ቢያንስ እንኮን መፀለያ ጊዜና ቦታ አለ ማለት ነው ::
ሌላው በማርቆስ ወንጌል 16:16 '' ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል '' ይላል ይሕም ማለት እኛ በሥላሤ ያመንን በሲኦል ካለው እሳት ልንድን እንችላለን ማለት ነው ::
ለምሳሌ ያክል በላየሰብ ለብዙ ዘመናት የሰኦችን ስጋ ሲበላ የነበረ ሰው ነው :: ከለታት በአንድ ቀን ሕይወቱ ያልፍና በሕይወት ሳለ በእመቤታችን ስም ቀዝቃዛ ውሀ ስላጠጣ በእመቤታችን አማላጅነት ከሲኦል ተረፈ እንግዲሕ በክርስቶስ ያላመነው በላየሰብ ከሲኦል እሳት ከዳነ እኛ በሥላሤ ያመንን ባርባ ቀንና በሰማኒያ ቀናችን የተጠመቅን በፃድቅ ሰው ስም ቀዝቃዛ ውሀ እንኮን የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይከፋም የሚለውን ቃል መሠረት አድርገን በፃድቅ ስም ዝክር የዘከርን ከሲኦል እሳት እንድናለን ማለትነው ::

ነገር ግን ሰው ሆይ

'' አንተ ግን በተማርክበትና በተረዳህበት ነገር ፀንተህ ኑር ''

2ኛ ጢሞ 3:14

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ