መንፈሳዊ


የአብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር 

የአብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር ነው::

 ገብርኄር ትርጉሙም ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው ::
 በዚሕ ሠንበት ከአለቃቸው ሶስት መክሊት ስለተዋሱት አገልጋዮችና ታማኝ አገልጋይ ስለተባለው አገልጋይ በማቴ 25 : 14 - 31 ላይ ያለው ታሪክ ይሰበክበታል 
:: 
የገብርኄር  የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
  መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኲሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባእ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ፡፡

 ትርጉም:- ጌታው በመልካም ሥራ የሚያገኘው በሐብቱ ኹሉ ላይ የሚሾመው፤የታመነ በጎ አገልጋይ ማን ነው? ዳግመኛም እግዚአብሔር አንተ የታመንክ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለኾንህ በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ይለዋል፡፡


 የገብርኄር የቅዳሴ ምንባባት :-

 2ኛ ጢሞ 2:1 - 16 
1ኛ ጼጥ 5 : 1 -16
 ግብረ ሐዋሪያት 1 : 6 - 9 

 የገብርኄር ምስባክ 
 ከመ አንግር ፈቀደከ መከርከ አምላከየ
 ወሕገከኒ በማዕከለ ከርስየ 
ዜናኩ ፅድቅከ በማኅበረ ዐቢይ 

 ወንጌልዘማትዎስ 25:14 - 31

 የገብርኄር ቅዳሴ 

 ቅዳሴ ዘባስልዩስ /እግዚአብሔርነ ክርረስቶስ /


 ወንድሞችና እሕቶች ሆይ ከእግዚአብሔር የተሰጠንን መክሊት በተገቢው መንገድ እንጠቀም ታማኝ አገልጋይ እንደተባለው እንደ ገብርኄር እናትርፍበት

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ