ሰኞ 5 ኦክቶበር 2015

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስለእሬቻ ኦዳ አመጣጥ ከመሰረቱ... "

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስለእሬቻ ኦዳ አመጣጥ
ከመሰረቱ...
"..በስምንት ሺህ ዓመተ ዓለም አካባቢ የኩሽ ልጆች
ሴታና ኦራ ተጣልተው ታላቁ ሴታ ታናሹን ኦራን ገደለ
...እህታቸው አቴቴ የወንድሟን አስክሬን በሌሊት አንስታ
አባይ ወንዝ ዳር ቀብራ አምላኳ ሰላም እንዲያወርድ
ተማፅና የመታሰቢያ ዋርካ ተከለች። የኩሽ አምላክም
ዝናብ አዝንቦ ዋርካውን አሳደገው፣ በዚህም ሰላም ሰፈነ
..ከአርባ ዓመት በኋላ የአቴቴ ልጆች የነበሩት ቦረና እና
ባሬንቱ እንደገና ተጣሉ። ታላቁ ቦረና ታናሽ ወንድሙን
ባሬንቱን ገደለው። እናታቸው አቴቴም አምርራ አዘነች።
የልጇን አስክሬንም በሌሊት ቀብራ ዋቃ-"እግዚአብሔር/
አላህ" ዘላቂ እርቀ ሰላም እንዲያወርድላት አምላኳን
ተማፀነች። ዋቃም ለመናዋን ሰማ፣ ኦዳ እንድትተክልም
አዘዛት። ልጆቿም የሚዳኙበት አዲስ ስርዓት ነገራት።
ያንንም የሰላም ትንሣኤ ሕይወት ገዳ ስርዓት አለው።
ጥንታዊና መሰረታዊ እምነቱ ደግሞ ዋቄፈና ተባለ። ኢሬቻ
ይህ ስርዓት የሚከበርበት በዓል ነው። <<የአፍሪካዊያን
እናት አቴቴ የአምላኳን ትእዛዝና በረከት ተቀብላ በወንዙ
ዳር ለዳር ኦዳ ተከለች። ወዲያው ዝናብ ዘነበ፣ ኦዳዎቹም
አደጉ ዘላቂ እርቅ ሰላምም በልጅ ልጆቹ ሕይወት ላይ
ወረደ። ያ የቅድስቷ የኦሮሞ እናት አድባር የሰላም የእርቅ
ቀን <<ኢሬቻ>> ተብሎ ይከበራል።
(ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ቀዌሳ፤ ገዳ መፅሔት)"

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ