የጅራፍ ንቅሳ
ከጀርባህ ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛ የመውደድድህ የዘላለም እትራት
የፋሪስ የሳዱቅ ያለማመን ደባ
-የጲላጦስ ግርፊያ የኤሮድስ ካባ
ከፊትህ የውጣው የደም ጎርፍና እምባህ
ላንተ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደ ስ ታህ
መከራህ ነውና የመዳን አሌንታህ
የመዳን አሌንታህ
ጅራፍና ቡጢ ምራቅና ሀሞት
ለዓይን ደስ የማይል የስቃይ ደምግባት
በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት
እንዲህ ናቸው ውበት የጌታ ደምግባት
የመዳን አሌንታ የዘላለም እትራት
ውዴ ይሄንን ያላያቹ
እኔ ልንገራቹ
ፍቅሩን ላሠማቹ
ምራቅ ተቀብቷል
ቡጢ ተቀብሏል
አጢያት ተሸክሟል
በቁንዳላው መሀል የደም ጎርፍ ይፈሳል
የፍቅር ንጉስ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል
ውድ ይሄን ያላያቹ
ድምጹን ላሠማቹ
ፍቅሩን ልንገራቹ
ዓይኑ ፍቅር ያለቅሳል
ጎኑ ደም ይረጫል
ፅሕሙ ተነጭቷል
ልብሱ ሜዳ ወድቋል
በቃሉም ቅዱስ ነው
ይቅርታን ይሠዋል ::
ከፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሣት
እኛን የመውደዱ የዘላለሙ እትራት
ለርሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን ሀሌንታ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ለሠው ልጆች ድፍረት ክብሩን አይቀንስም
ስለሠው መድከሙን ኃይሉን አያወርድም
ስሙ እግዚአብሄር ነው
ስሙ ይቅርታ ነው
ስሙ መሀሪ ነው
የፈረሱን ብርታት ብቃቴ ነው የሚል
ብዛቱን ተማምኖ የሚታበይ ልዑል
በሱ ስም ይወድቃል
በስሙ ይጣላል ::
ስሙ ሁልን ቻይ ነው ሁሉንም አድራጊ
ታላቁን 'ሚጥል ለታናሽ ተዋጊ
ውድ ይሄን ያላያቹ
ድምጹን ያልሰማቹ
እኔ ልንገራቹ
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሣት
እኛን የመውደዱ የዘላለም እትራት
ለሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን ሀሌንታ
.
.
.
እናም ጌታችን ሆይ
ያመኑክ ይጽናኑ
የውጉሁም የዩህ
በደም የተረጩ ልብሶችሕን ለብሠህ
አሜን ______ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሠህ ::
ኤፍሬም ስዩም በኦዲዮ ሢዲ ካሣተመው የግጥም አልበም ውስጥ
አሜን ______ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሠህ ::
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ