ንቡረእድ ክፍለ ዮሐንስ መኮንን ዐረፉ
ንቡረእድ ክፍለ ዮሐንስ መኮንን ከአባታቸው ከአቶ መኮንን ደስታ
እና ከእናታቸው ከወለተ መድኅን በወሎ ክፍለ ሀገር በዋግ
አውራጃ ጻግብች ወረዳ ልዩ ስሙ በለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተባለ
ቦታ በ1931 ዓ.ም ተወልደው
ትምሕርታቸውን
ከንባብ እስከ ጸዋትወ ዜማ በተወለዱበት ደብር በበለቃ ቅዱስ
ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተምረዋል፡፡
ከብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በ1944 ዓ.ም. ዲቁና ተቀብለው በበለቃ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል፡፡
ላስታ አውራጃ በመሔድም ከታላቁ መምህር ከየኔታ በጻህ ዘንድ
ቅኔ ተቀኝተዋል፡፡
በራያና አዘቦ ልዩ ስሙ አንጎት መድኃኔዓለም ደብር ከታላቁ ሊቅ
ሊቀ ኅሩያን ወልደ ሰንበት ዘንድ ለሰባት ዓመታት በመቆየት ቅኔን
ከነአገባቡ በሚገባ ተምረው አስመስክረዋል፡፡
በጎንደር ክፍለ ሀገር ወገራ አውራጃ ጎንትር አባ ከየኔታ ብዙአየሁ
የየኔታ ገሞራውን አገባብ ቀጽለውና ጽፈው ጨርሰዋል፡፡
በጎጃም ክፍለ ሀገር ከመጽሐፉ ሊቅ ከየኔታ ዲበኩሉ የትርጓሜ
መጻሕፍትን ተምረው አጠናቀዋል፡፡ እንዲሁም የቅኔ አገባቡን
በድጋሚ ተምረዋል፡፡
ወደ ዋሸራ በማምራትም ለተወሰኑ ወራት ቅኔ አጥንተዋል፡፡
በደብረ ማርቆስ ከመምህር ጥበቡ ካሳ ከተባሉ ገናና የቅኔ
መምህር ቅኔ ተምረዋል፡፡
ንቡረእድ ክፍለ ዮሐንስ መኮንን ሕይወታቸው እስካለፈበት
ማለትም ሚያዚያ 11ቀን 2007 አ ም ድረስ ታከተኝ ሰለቸኝ
ሳይሉ ቅድስት ቤተክርስትያንን አገልግለዋል ንቡረእድ ክፍለ
ዮሐንስ መኮንን
፦ በአዲስ አበባ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
በቅኔ
መምህርነት
፦ በሽሮ ሜዳ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን
የየደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ገብረ ክርስቶስ አብያተ
ክርስቲያናት በአስተዳደሪነት
፦ በጅጅጋ ደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፤
በብርሃናተ
ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን፤ በደብረ
ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን፤ በናዝሬት ደብረ ፀሐይ
ቅድስት ማርያም ካቴድራል በአስተዳደሪነት
በሰሜን ሸዋ የሰላሌ ሀገረ ስብከት፤ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ
ስብከት፤ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
በመሆን ቤተ ክርስቲያንን
፦ ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ
ከፍተኛ
መንፈሳዊ ኮሌጅ ሕወታቸው እሰካለፈበት ቀን በበምህርነት
ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ንቡረእድ ክፍለ ዮሐንስ መኮንን በተለይ ሙሉ ጊዜአቸውን
በቅንኔ መምሕርነትና በድጔ በአቋም መምሕርነት ሲያገለግሉ
ነበር።
ሊቁ ንቡረአድ ክፍለ ዮሐንስ መኮንን ሁለት ወንዶችና ሁለት
ሴች ልጆችን በተቀደሰ ጋብቻ አፍርተዋል፡፡
ንቡረእድ ክፍለ ዮሐንስ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በቅዱስ
ጳውሎስ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ ቆተው በተወለዱ በ76
ዓመታቸው ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ
ሥጋ ተለይተዋል፡፡
ሚያዝያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅሰድስት
ሥላሴ ካቴድራል ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤
የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው፤ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ምእመናን
በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡
የአባታችንን ነፍስ ከቅዱሳን አባቶቻችነ ነፍስ ጋር ይደምርልን
ሐሙስ 23 ኤፕሪል 2015
ንቡረእድ ክፍለ ዩሐንስ ዐረፉ
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ