.እስከ ማዕዜኑ ..እስከ ማዕዜኑ አነብር ውስተ ልብየ ትካዘ
ዐሊውየ ሕገ ወትዕዛዘ ማርያም ኩነኒ መናዝዘ ።
አቤል በፀጋ ርቆ ፣ በየዋህነት ከመጠቀበት ፣
ቃዬል በንፍገት ከብሮ ፣ መቀመቅ ከወረደበት ፣
የዕጓለመሕያው ታሪክ ፣ ሲጀመር የጠቆረበት .
እንውረድ ብሎት ወንድሙን ፣ እስትንፋሱን የነጠቀበት ፣
ኃዘና ፣ ስምዒ ወብካያ ፣ለሃገሪትነ ኢትዮጵያ ።
የሞት ታሪክ ሊዘከር
በአዝማናት ማሀል ሊነገር
የመጀመሪያው መልአክ ፣ ታሪኩን ሲፅፈው እንደዚህ ነበር።
ክልዔቱ አኃው መንገደ ቀላይ ወረዱ፣
እኒህ ሁለት ወንድሞች ወደ አዘቅት የሄዱ፣
አንደኛው ሟች ሊሆን ገዳይ ሊሆን አንዱ፣
አሃዱ ተመይጠ፣ ወኢተመይጠ አሃዱ ፣
አንደኛው ሲመለስ ሁለተኛው እዚያው የቀረ፣
ውረድ እንውረድ ያለው ወንድሙ ገድሎት ነበረ።
ከዚህ የቀን ጎደሎ ነው ፣ ከዚህ ክህደት በኋላ፣
ከተራራው አናትና ከግርጌ በቆመው ማሀል መተማመኑ የላላ።
የአዳም የልጅ ልጅ ሁሉ ምን ቢጀግን ምን ቢያቅራራ፣
ምን ደግ ንግርት ቢያስነግር ፣ ምን በማዕረግ ቢጠራ ፣
ይገሉኝ ይሆን እያለ ነው ፣ ውረድ ሲሉት የሚፈራ ።
እናም መውረድ ሞቱ ነው አንዴ ደርቡን ከወጣ ፣
ውረድ ሲባል በመውረዱ ነው ፣ ወንድሙ ሕይወቱን ያጣ።
በርግጥ ለምን ይወርዳል መውረድስ ማንን ጠቀመ ?
የወረደውን መግደሉ ለዘላለሙ ካልቆመ !
----------
አበባው መላኩ - "ደግ አይበረክትም" ከተሰኘው ሲዲ ቅንብር
የጠገለበጠ
ማክሰኞ 21 ኤፕሪል 2015
አበባው መላኩ - "ደግ አይበረክትም"
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ